Showing the last 7 days. Upgrade to Pro for the full archive.
Announcement
2026-09-14 Abiy Ahmed

በ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ የነበረን ቆይታ ቅኝት፦ ‎አዲሱን ዓመት የጀመርነው ስትራቴጂካዊ ጥቅሞቻችን በተረጋገጡበት እና የአፍሪካ ድምፅ በዓለም አቀፍ መድረክ ከፍ ባለበት ታሪካዊ ስኬት ነው! ‎ ‎ 🇪🇹

Announcement
2026-09-13 Abiy Ahmed

Economic uncertainty is testing our countries. BRICS has already reshaped the global conversation. Our responsibility now is to help shape a fairer international system and widen economic opportunity.

Announcement
2026-09-13 Abiy Ahmed

የብሪክስ ጉባኤ ሁለተኛው ቀን ላይ ከካዛኪስታን ፕሬዚዳንት ቃሲም ጆማርት ቶካዬቭ ጋር የሁለትዮሽ ውይይት አድርገናል። ‎በዲጂታላይዜሽን፣ በንግድና ኢንቨስትመንት እንዲሁም በመከላከያ መስኮች የትብብር ዕድሎችን ለማስፋት እና ‎በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን አጋርነት ይበልጥ ማሳደግ በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ መክረናል። 🇪🇹 🇰🇿

Announcement
2026-09-13 Abiy Ahmed

በብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጋር የተደረገ ውይይት። 🇪🇹 🇨🇳

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

ጽናትን፣ ፈጠራን፣ ትብብርን እና ዘላቂነትን መገንባት በሚል መሪ ቃል በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ በሚገኘው 18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ላይ አካል በመሆናችን ኩራት ይሰማናል። ‎ ‎በብሪክስ አባል ሀገራት ዘንድ ሀብት፣ ቴክኖሎጂ እና ሰፊ ገበያ አለን፤ አሁን ያለው መልካም ዕድል እነዚህን አቅሞች በማስተሳሰር የላቀ እሴት መፍጠር እና ይህ እሴት ደግሞ ሀብቱ በሚገኝበት ቦታ መመረት እንዲችል ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ በማዕድን ልማት፣ በታዳሽ ኃይል እና እያደገ በሚገኘው የኢንዱስትሪ መሠረቷ ላይ እነዚህን አጋርነቶች ለመገንባት ዝግጁ ናት። ‎ ‎በተጨማሪም በአሠራር ሥርዓቶቻችን ውስጥ ጽናትን መገንባት፣ የሰው ሰራሽ አስተውሎት የአህጉራችንን ፍላጎት እንዲያገለግል ማድረግ፣ አስተማማኝ የዕዳ እፎይታ ሒደትን ማሳደግ እንዲሁም የአየር ንብረት ጥበቃ ሥራዎችን ከኢኮኖሚ ሽግግር ጋር ማስተሳሰር ይኖርብናል። ‎ ‎የብሪክስ መድረክ የጋራ ትብብርን ወደ የጋራ እሴት፣ ጽናት እና ዘላቂ ዕድገት የመለወጥ ሰፊ አቅምና ቁርጠኝነት አለው።

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

ከ18ኛው የብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን፣ ከአቡ ዳቢ አልጋ ወራሽ ከልዑል ሼህ ኻሊድ ቢን ሙሀመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን ጋር መክረናል። ‎በቆይታችንም በዋና ዋና የብሪክስ ቅድመ-አጀንዳዎች እና በኢትዮጵያና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል ያለውን ሁለገብ ትብብር የበለጠ በሚያጠናክሩ ሂደቶች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ‎ 🇪🇹 🇦🇪

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

ከፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ተገናኝተን በኢትዮጵያ እና ሩሲያ መካከል ያለውን ስትራቴጂካዊ አጋርነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። ‎ ‎ውይይታችን በመከላከያ እና ደኅንነት፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በትምህርት እንዲሁም በቴክኖሎጂ መስኮች ያለንን ትብብር ለማሳደግ ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋገጥንበት ነው። እንዲሁም የትምህርት ልምድ ልውውጦችን ማስፋት፣ በባህል እና በሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ያለንን ትብብር ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎በተጨማሪም ለኮፕ 32 በምናደርገው ዝግጅት ያለንን አጋርነት ጨምሮ ፣ በአየር ንብረት ለውጥ እና በልማት ግቦች ዙሪያ ትብብሮችን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታዎች ላይ ተወያይተናል። በወል ተጠቃሚነት ላይ የተመሠረቱ የንግድ እና የኢኮኖሚ ልውውጦችን ይበልጥ ለማስፋፋትም በጋራ ለመሥራት ተስማምተናል። ‎ 🇪🇹 🇷🇺

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን የቪየትናም ጠቅላይ ሚኒስትር ሌ ሚን ሁንግን አግኝቸ ፍሬያማ ውይይት አድርገናል። በኢትዮጵያ እና ቪየትናም መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር እና የጋራ ትብብራችንን ማስፋት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎ 🇪🇹 🇻🇳

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

በሕንድ ይፋዊ የሥራ ጉብኝቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ጋር በመገናኘት፣ የኢትዮጵያ-ሕንድ አጋርነትን ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ፍሬያማ ሃሳብ ተለዋውጠናል። ‎ ‎ውይይታችን የመከላከያ ትብብርን ማሳደግ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ የአቅም ግንባታ፣ የማዕድን ልማት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን አጋርነት ማጠናከር በሚሉ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነበር። እነዚህ መስኮች በተግባር የታገዘ ትብብራችንን ይበልጥ ለማሳደግ እና ለሕዝቦቻችን አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር ከፍተኛ አቅም አላቸው። ‎ ‎ኢትዮጵያና ሕንድ ጥልቅ ታሪካዊ ትስስር፣ የዘመናት የባህል ግንኙነት እና በሕዝቦቻችን መካከል ጠንካራ ወዳጅነት አለን፤ ይሁን እንጂ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያሉት በርካታ አቅሞች ገና ያለተነኩ ናቸው። ያለንን የጋራ ታሪክና ትብብር በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት፣ በኢንቨስትመንት፣ በዘላቂ ልማት እና ይበልጥ በጠነከረ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ላይ ወደተመሠረተና የላቀ የጋራ ተጠቃሚነትን ወደሚያረጋግጥ አጋርነት ለመለወጥ አሁን ትክክለኛው ጊዜ…

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

በብሪክስ ፕላስ የቤተሰብ መድረክ ማዕቀፍ ውስጥ፣ ከኢራኑ ፕሬዚዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ጋር ተወያይተናል። ‎ ‎ከጉባኤው ጎን ለጎን ባደረግነው ውይይት በቀይ ባሕር አካባቢ ባሉ ወቅታዊ ሁነቶች እና አጠቃላይ በቀጣናው የደኅንነት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ሲሆን፣ የውይይትን አስፈላጊነት እና የቀጣናውን መረጋጋት እውን ማድረግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያም መክረናል። 🇪🇹 🇮🇷

Announcement
2026-09-12 Abiy Ahmed

ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተናኝተን መክረናል። ‎ ‎በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል። ‎ ‎ውይይታችን ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል። ‎ ‎ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው። 🇪🇹 🇲🇾

Announcement
2026-09-10 Abiy Ahmed

Ethiopia's journey to the African Free Trade Zone: a work built in practice Today at Mojo, we inaugurated the first phase of the expansion of a modern logistics center built on 60 hectares of land, which will play an important role in the success of Ethiopia and Africa's continental free trade zone. This huge project has stations and modern warehouses with the capacity to handle up to 1 million 20-foot containers per year, enabling us to pack dry dust loads in the country, not only saving foreign currency, but also creating ample job opportunities for our citizens. In order to increase the wor…

Announcement
2026-09-10 Abiy Ahmed

Tomorrow's day National technology transfer From paper to digital; From user to creator! Digital transformation is becoming our daily culture by learning and correcting yesterday and building today with greater diligence. Streamlines business and services, makes information accessible, and updates sectors! The movement of 5 million Ethiopian coders is moving towards our goal of 7 million by making young people creators of artificial intelligence and has ensured the accessibility and quality of digital services. Our cyber sovereignty, which is rich in indigenous capabilities, and has stopped re…

Announcement
2026-09-09 Abiy Ahmed

Union Day Our Ethiopia with its indigenous values; She is shaping her bright future with her own hands! We have laid an unshakable foundation for our strong national unity by enhancing our wonderful indigenous values ​​and being guided by the philosophy of inclusion. From the beginning of the history of starting the historic national consultation, from our people-oriented corridor development, our voluntary work and the realization of the Green Footprint program that will change the lives of all our citizens; We have demonstrated in practice that when we all stand together, our common stories …

Announcement
2026-09-08 Abiy Ahmed

Endurance Day When we think of Ethiopia, it is impossible to think about universal elevation without giving priority to our strong security forces who stand steadfast day and night to protect the country from the enemy. That is why on this Endurance Day, we commemorate the historical sacrifice of our heroes who gave their precious lives for the permanence and sovereignty of our country with great national honor. Today, our country has been able to produce high-tech unmanned aerial vehicles, modern armored military vehicles, heavy weapons and artillery, as well as ammunition through its own mil…

Earlier quotes are Pro-only

Free access covers the last 7 days. Unlock the full historical archive with Pro.

Sign up for Pro

Already a member? Log in