Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Union Day Our Ethiopia with its indigenous values; She is shaping her bright future with her own hands! We have laid an unshakable foundation for our strong national unity by enhancing our wonderful indigenous values and being guided by the philosophy of inclusion. From the beginning of the history of starting the historic national consultation, from our people-oriented corridor development, our voluntary work and the realization of the Green Footprint program that will change the lives of all our citizens; We have demonstrated in practice that when we all stand together, our common stories can lead us to common success. We are not only building an inclusive, economically independent, strong country with a culture of solidarity and cooperation, but we are also affirming the common greatness and potential of all Ethiopians. Together we will continue our journey to prosperity. One nation, one great country, Ethiopia! #EthiopiaPrevails
Notes
የኅብር ቀን ኢትዮጵያችን በሀገር በቀል እሴቶቿ፤ የነገውን ብሩህ ተስፋዋን በገዛ እጆቿ እየቀረጸች ትገኛለች! በትውልድ ቅብብሎሽ ያገኘናቸውን ድንቅ የሀገር በቀል እሴቶቻችንን በማጎልበት እና በመደመር ፍልስፍና በመመራት፣ ለጽኑ ኅብረብሔራዊ አንድነታችን የማይናወጥ መሠረት ጥለናል። ታሪካዊውን ሀገራዊ ምክክር የመጀመር የታሪክ እጥፋት ተነስተን፣ የሁሉም ዜጎቻችንን ሕይወት ከሚለውጡ ሰው-ተኮር የኮሪደር ልማታችን፣ የበጎ ፈቃድ ስራዎቻችን እንዲሁም የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃግብርን በተግባር እውን እስከማድረግ ድረስ፤ ሁላችንም በአንድነት ስንቆም የጋራ ትርክቶቻችን ወደ ጋራ ስኬት እንደሚያሻግሩን በተግባር አሳይተናል። እኛ የምንገነባው አካታች የሆነች፣ በኢኮኖሚ ራሷን የቻለች፣ የአብሮነትና መረዳዳት ባህል የጎለበተባት ጠንካራ ሀገር ብቻ ሳይሆን የሁሉንም ኢትዮጵያውያን የጋራ ታላቅነትና እምቅ አቅም በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። በአንድነት ወደ ብልጽግና ጉዟችን እንቀጥላለን። አንድ ህዝብ፣ ታላቅ ሀገር ኢትዮጵያ! #EthiopiaPrevails