Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-09-10 05:02

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Tomorrow's day National technology transfer From paper to digital; From user to creator! Digital transformation is becoming our daily culture by learning and correcting yesterday and building today with greater diligence. Streamlines business and services, makes information accessible, and updates sectors! The movement of 5 million Ethiopian coders is moving towards our goal of 7 million by making young people creators of artificial intelligence and has ensured the accessibility and quality of digital services. Our cyber sovereignty, which is rich in indigenous capabilities, and has stopped relying on technologies that we do not control, proudly announces that the new Ethiopia, which stands on its own in the digital economy, is at a great stage! #DigitalEthiopia2030

Notes

የነገው ቀን ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሽግግር ከወረቀት ወደ ዲጂታል፤ ከተጠቃሚነት ወደ ፈጣሪነት! ትናንትን በመማርና በማረም ዛሬን በላቀ ትጋት በመገንባት ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የዕለት ተዕለት ባህላችን እየሆነ ነው። ንግድና አገልግሎትን ያቀላጥፋል፣ መረጃዎችን ተደራሽ ያደርጋል፣ ዘርፎችንም ያዘምናል! የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያ ኮደሮች ንቅናቄ ወጣቶችን የሰው ሰራሽ አስተውሎት ፈጣሪ በማድረግ ወደ 7 ሚሊዮን ግባችን እያመራ ሲሆን የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን አረጋግጧል። በሀገር በቀል አቅም የበለጸገው የሳይበር ሉዓላዊነታችን ደግሞ የማንቆጣጠራቸው ቴክኖሎጂዎችን ጥገኝነት አላቆ በዲጂታል ኢኮኖሚ በራስ አቅሟ የምትቆም አዲሷ ኢትዮጵያ በታላቅ ምዕራፍ ላይ መሆኗን በኩራት ያበስራል! #DigitalEthiopia2030