Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Endurance Day When we think of Ethiopia, it is impossible to think about universal elevation without giving priority to our strong security forces who stand steadfast day and night to protect the country from the enemy. That is why on this Endurance Day, we commemorate the historical sacrifice of our heroes who gave their precious lives for the permanence and sovereignty of our country with great national honor. Today, our country has been able to produce high-tech unmanned aerial vehicles, modern armored military vehicles, heavy weapons and artillery, as well as ammunition through its own military industries with its own knowledge and the capabilities of its children. Since this self-reliance is the solid foundation of our people's peace and universal economic development, we will strengthen Ethiopia's lasting prosperity by ensuring our national stability through real development and a strong ability to protect and defend! #EthiopiaPrevails
Notes
የጽናት ቀን ኢትዮጵያን ስናስብ፣ ሌት ተቀን በጽናት በመቆም ሀገርን ከጠላት ለመጠበቅ ወጥተው ለሚያድሩት ብርቱ የፀጥታ ኃይሎቻችን ቅድሚያ ሳንሰጥ ስለ ሁለንተናዊ ከፍታ ማሰብ ፈጽሞ አይቻልም፡፡ ለዚህም ነው በዚህ የጽናት ቀን፣ ለሀገረ-መንግሥታችን ዘላቂነትና ሉዓላዊነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የከፈሉትን የጀግኖቻችንን ታሪካዊ መስዋዕትነት በከፍተኛ ሀገራዊ ክብር የምንዘክረው፡፡ ዛሬ ላይ ሀገራችን በራሷ ዕውቀትና በልጆቿ አቅም የላቀ የቴክኖሎጂ ብቃት ያላቸውን ሰው አልባ አውሮፕላኖችን፣ ዘመናዊ የታጠቁ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን፣ ከባድ መሣሪያዎችንና መድፎችን፣ እንዲሁም ተተኳሽ ጥይቶችን በራሷ ወታደራዊ ኢንዱስትሪዎች ማምረት ችላለች፡፡ ይህ በራስ የመቆም አቅም፣ የሕዝባችን ሰላምና የሁለንተናዊ ኢኮኖሚ እድገታችን ጽኑ መሠረት በመሆኑ፣ ሀገራዊ ጽናታችንን በተጨባጭ ልማትና በጠንካራ የመጠበቅና የመከላከል አቅም እያረጋገጥን የኢትዮጵያን ዘላቂ ብልጽግና እናጸናለን! #EthiopiaPrevails