Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
ከብሪክስ ጉባኤ ጎን ለጎን ከማሌዢያ ጠቅላይ ሚኒስትር አንዋር ኢብራሂም ጋር ተናኝተን መክረናል። በሕዳር 2018 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ካደረጉት ታሪካዊ ጉብኝት የተገኘውን መልካም ዕድል ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተናል። ውይይታችን ኢንቨስትመንትን፣ ቱሪዝምን፣ የታዳሽ ኃይል አጋርነትን ማስፋፋት እና ወደ ኮፕ 32 በሚደረገው ጉዞ ላይ ያለንን ትብብር ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም በማሌዢያ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ ምርታማነት እና የአምራች ዘርፍ ተሞክሮዎችን መውሰድ በሚቻልባቸው ዕድሎች ዙሪያ መክረናል። ኢትዮጵያና ማሌዢያ ጠንካራ የኢኮኖሚ አጋርነት ለመመስረት የሚያስችል ከፍተኛ አቅም አላቸው፤ ይህም በኢንቨስትመንት፣ በቴክኖሎጂ፣ በክህሎት እና በዘላቂ ልማት ማዕቀፎች አዳዲስ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው። 🇪🇹 🇲🇾
Notes