Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
It is impossible to see Ethiopia separately from its youth! As the age composition of our population indicates, the fact that young people have the largest number is a great opportunity to ensure and sustain prosperity. Ethiopia's youth is the main engine of change and the strong point of our sovereignty! Ethiopian youth is writing the history of the country with a new pen and paper. Today's youth has focused on development and avoided poverty by avoiding the customs, unnecessary arguments, arguments and conflicts that have kept our country backward. The Government of Adder is working with focus and determination to strengthen the universal benefit and leadership role of the youth. I call on all of you to be active and walk in love to realize our national goal.
Notes
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም! የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው። የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል። የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል። ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።