Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-08-11 06:32

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Friendship Park in the center of Addis Ababa is one of the first multi-purpose public facilities built by the government in the last eight years. ‎ This park has generated an income of about one billion birr in the last four years alone, and has directly and indirectly created job opportunities and economic benefits. Above all, it has become a meeting place for citizens and visitors from different walks of life. From families and children, sports teams and wedding attendees to digital content creators, as well as local and international visitors, there are many in attendance. Apart from its economic value, Friendship Park is providing a great service for health, fitness, recreation and social connection. This is proof of how well-planned public facilities can connect people while contributing to the overall urban development of Addis Ababa. ‎ This park is a precedent for similar public facilities being built in the city as well as other cities. These new places are centers that create value, facilitate opportunities and most importantly, ensure Ethiopian ownership.

Notes

በአዲስ አበባ መሐል የሚገኘው የወዳጅነት ፓርክ ባለፉት ስምንት ዓመታት በመደመር መንግሥት ከተገነቡት የመጀመሪያዎቹ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የሕዝብ መገልገያ ቦታዎች አንዱ ነው። ‎ ‎ይህ ፓርክ ባለፉት አራት ዓመታት ብቻ ወደ አንድ ቢሊዮን ብር ገደማ ገቢ ያስገኘ ሲሆን፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሥራ ዕድሎችንና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ፈጥሯል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ከተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች የተውጣጡ ዜጎችና ጎብኝዎች የሚገናኙበት ሥፍራ መሆን ችሏል። ከቤተሰቦችና ሕፃናት፣ ከስፖርት ቡድኖችና ከሠርግ ተካፋዮች ጀምሮ እስከ ዲጂታል ይዘት ፈጣሪዎች፣ እንዲሁም የሀገር ውስጥና የውጭ ሀገር ጎብኚዎች በቦታው ይገኙበታል። የወዳጅነት ፓርክ ከኢኮኖሚያዊ እሴቱ ባሻገር ለጤና፣ ለአካል ብቃት፣ ለመዝናኛና ለሕብረተሰብ ትስስር ትልቅ አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤ ይህም በጥሩ ሁኔታ የታቀዱ የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ለአዲስ አበባ ከተማ አጠቃላይ የከተማነት ዕድገት አስተዋጽኦ እያበረከቱ ሰዎችን እንዴት ማገናኘት እንደሚችሉ ማረጋገጫ ነው። ‎ ‎ይህ ፓርክ በከተማዋ እንዲሁም በሌሎች ከተሞች ውስጥ እየተገነቡ ላሉ ተመሳሳይ የሕዝብ መገልገያ ሥፍራዎች ቀዳሚ ማሳያ ነው። እነዚህ አዳዲስ ቦታዎች እሴት የሚፈጥሩ፣ ዕድሎችን የሚያመቻቹ እና ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢትዮጵያውያንን ባለቤትነትን የሚያረጋግጡ ማዕከላት ናቸው።