Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Today we inaugurated the new terminal of Bahir Dar Dejazmach International Airport. It is a big milestone for this airport, which is one of the key flight gateways for Ethiopia. This project means more than a modern terminal. After the trials that Bahr Dar has faced in recent times; The completion and commissioning of this terminal is proof of resilience, resilience and continued investment. The new terminal includes spacious aircraft stands, advanced infrastructure, improved access roads and modern facilities. This will meet the growing needs of the area by increasing the capacity of the airport and provide convenient and efficient services to passengers. This new terminal coupled with the urban transformation that is renovating the city; It makes Bahrain another key destination and hub for international and domestic flights. I hope the local community will continue to maintain peace to ensure the economic benefits of a vibrant city like Bahrain.
Notes
ዛሬ የባህር ዳር ደጃዝማች በላይ ዘለቀ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ አዲሱን ተርሚናል መርቀናል። ለኢትዮጵያ ቁልፍ የበረራ በሮች አንዱ ለሆነው ለዚህ አውሮፕላን ማረፊያ ትልቅ ምዕራፍ ነው። ይህ ፕሮጀክት ከዘመናዊ ተርሚናል በላይ ትርጉም አለው። ባህር ዳር በቅርብ ጊዜያት ካስተናገደቻቸው ፈተናዎች ማግስት፤ የዚህ ተርሚናል ግንባታ ተጠናቆ አገልግልት መጀመር የፅናት፣ የማገገም እና ቀጣይነት ያለው ኢንቨስትመንት ማረጋገጫ ነው። አዲሱ ተርሚናል ሰፊ የአውሮፕላን ማቆሚያዎችን፣ የላቁ መሰረተ ልማቶችን፣ የተስተካከሉ መዳረሻ መንገዶችን እና ዘመናዊ መገልገያዎችን ያካተተ ነው። ይህም የአውሮፕላን ማረፊያውን የመቀበል አቅም በማሳደግ የአካባቢውን እያደገ የመጣ ፍላጎት የሚያሟላ ሲሆን፣ ለመንገደኞችም ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት ይሰጣል። ይህ አዲስ ተርሚናል ከተማዋን እያደሰ ካለው የከተማ ትራንስፎርሜሽን ጋር ተዳምሮ፤ ባህር ዳርን ለዓለም አቀፍ እና ለሀገር ውስጥ በረራዎች ሌላኛዋ ቁልፍ መዳረሻና ማዕከል ያደርጋታል። ባህር ዳርን የመሰለች ንቁ ከተማ የምታስገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ለማረጋገጥ የአካባቢው ማህበረሰብ ሰላሙን መጠበቁን እንደሚቀጥል ተስፋ አደርጋለሁ።