Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-08-03 07:30

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Eight years. Continuous action! The Green Footprint program continues to grow stronger, driven by public commitment and the common belief that Ethiopians can build a green and sustainable tomorrow together. Today is our annual one-night national tree planting program where Ethiopians come together to leave a lasting mark that will survive for the next generation. Together with the First Lady Znash Tayah and the COP32 National Committee, we have contributed to this joint journey by leaving our mark. As we are working together to achieve the ambitious goal of planting 800 million saplings, I call on Ethiopians to continue your efforts throughout the day.

Notes

ስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር! የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በህዝባዊ ቁርጠኝነት እና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን አረንጓዴ እና ዘላቂነት ያለው ነገን መገንባት ይችላሉ በሚለው የጋራ እሳቤ እየተመራ ይበልጥ እየጠነከረ ቀጥሏል። ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ዐሻራ ለማሳረፍ በጋራ የሚሰባሰቡበት ዓመታዊው የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብራችን ነው። ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር እንዲሁም ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የራሳችንን ዐሻራ በማሳረፍ ለዚህ የጋራ ጉዞ የበኩላችንን አስተዋፅኦ አበርክተናል። የተቀመጠውን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ታላቅ ግብ ለማሳካት በጋራ እየሰራን በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ቀኑን ሙሉ ጥረታችሁ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።