Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-08-03 08:39

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Green footprint is one of the journey of prosperity! • Civilization is not the result of a single act; The development of one sector does not train alone • Our Green Footprint is not a one season campaign; It is not a short-term goal! • Green Footprint: Our biggest goal is to be smart. It is part of our journey of prosperity and overall development as a nation. Green footprint. Another foundation of civilization! • Civilization is not built in thin air; It needs a solid foundation. • What is built without a strong foundation is easily destroyed, it will not last. • A civilization that transcends the ages is known for its depth. Today's green footprint is one of the many foundations of civilization! • It is seen like energy development, industrial expansion, skill building etc. Ecological sustainability for a strong civilization • How we will build institutions to strengthen nation building; To strengthen our solidarity, we are working on national reconciliation and consultation. As we focus on industrial and digital sectors to bring about the structural transition of our economy; As we work on administrative excellence to strengthen the country and ownership of all of them; We should work on green footprint to bring ecological sustainability. • Because if solidarity is not maintained, if economic structural transition is not carried out, civilization will fail; • If the construction of the state is not strong, just as civilization will not last; Without ecological sustainability, civilization will not last. • The loss of one does not make civilization complete! Let's strengthen our foundation by planting hope!

Notes

አረንጓዴ ዐሻራ የመበልጸግ ጉዞ አንዱ ሰበዝ! • ሥልጣኔ የነጠላ ተግባር ውጤት አይደለም፤ የአንድ ዘርፍ እድገትም ብቻውን አያሰለጥንም • የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን የአንድ ሰሞን ዘመቻ አይደለም፤ የአጭር ጊዜ ግብን ታሳቢ ያደረገ ቁንጽል እርምጃ አይደለም! • አረንጓዴ ዐሻራ፦ የትልቁ ዓላማችን አንድ ሰበዝ ነው። እንደ ሀገር የመበልጸግና የሁለንተናዊ እድገት ጉዟችን አካል ነው። አረንጓዴ ዐሻራ፤ ሌላኛው የሥልጣኔ መሰረት! • ሥልጣኔ ባዶ አየር ላይ አይገነባም፤ ጠንካራ መሰረት ይፈልጋል። • መሰረት ሳይጸና የሚገነባ ነገር በቀላሉ ፈራሽ ነው፣ አይዘልቅም። • ዘመናትን የሚሻገር ስልጣኔ በመሰረቱ ጥልቀት ይታወቃል። የዛሬ አረንጓዴ ዐሻራ ከብዙ የሥልጣኔ መሰረቶች አንዱ ነው! • ልክ እንደ ኢነርጂ ልማት፣ የኢንደስትሪ ማስፋፋት፣ እንደ ክህሎት ግንባታ ወዘተ የሚታይ ነው። ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነት ለጠንካራ ሥልጣኔ • ሀገረ-መንግሥታዊ ግንባታን ለማጠናከር ተቋማትን እንደምንገነባው፤ አብሮነታችንን ለማጠናከር ሀገራዊ እርቅና ምክክር ላይ እንደምንረባረበው፤ የኢኮኖሚያችን መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ኢንዱስትሪና ዲጅታል ዘርፎች ላይ እንደምናተኩረው፤ የሁሉም ዐሻራ ያረፈባት ሀገርና ባለቤትነትን ለማጽናት አስተዳደራዊ ልህቀት ላይ እንደምንሰራው፤ ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነትን ለማምጣት አረንጓዴ ዐሻራ ላይ መስራት ይገባል። • ምክንያቱም አብሮነት ካልተጠበቀ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ካልተካሄደ ሥልጣኔ እንደማይሳካው፤ • ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ካልጠነከረ ሥልጣኔ እንደማይዘልቀው ሁሉ፤ ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነት ካልመጣ ሥልጣኔ አይዘልቅም። • የአንዱ መጉደል ሥልጣኔን ምሉዕ አያደርግም! ተስፋን በመትከል መሰረታችንን እናጽና!