Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
I am very proud to be present at the launch ceremony of this historic national consultation. This great conference, which will gather four thousand participants under one roof in the coming weeks, is a historic occasion where Ethiopia has found the "pen and paper" that will enable her to write a new history with her own hands. Ethiopia's political journey begins with strong words and ends with strong actions. I express my gratitude to the Commissioners of the National Consultative Commission for their contribution to the success of this great journey. This conference, which is based on the process of gathering the agenda from the bottom up involving hundreds of thousands of citizens, is not easily repeated and has a huge and great purpose in the modern history of Ethiopia. By turning our challenges into good opportunities, we will strengthen the culture of peaceful transition of power. Today we sow good seeds that will survive for the next generation. We will make our children benefit from the fruit it produces. When we participate in this consultation, when we come out of our neighborhood and advise Ethiopia, when we discuss for our children and thinking about them, the result will be very fruitful. Let's plant hope, forgiveness and coexistence together. Let's protect our country from outside interference by solving our problems through domestic dialogue and forgiveness. I invite all the participants to record a historic result that is good for Ethiopia, a teacher for Africa, and a real rest for all Ethiopians. Let Ethiopia be proud of her children's efforts and live forever!
Notes
በዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ ምክክር የማስጀመሪያ ሥነ-ሥርዓት ላይ ለመታደም በመታደሌ ታላቅ ኩራት ይሰማኛል። በሚቀጥሉት ሳምንታት አራት ሺህ ተሳታፊዎችን በአንድ ጣሪያ ስር የሚያሰባስበው ይህ ታላቅ ጉባኤ፣ ኢትዮጵያ በገዛ እጇ አዲስ ታሪክ ለመጻፍ የሚያስችላትን “ብዕርና ብራና” ያገኘችበት ታሪካዊ አጋጣሚ ነው። የኢትዮጵያ የፖለቲካ ጉዞ በኃይለ ቃል ጀምሮ በኃይለ እርምጃ የሚደመደምበትን አዙሪት ሰብረን በንግግርና በውይይት የምንተካበት ወቅት ላይ እንገኛለን። ለዚህ ታላቅ ጉዞ መሳካት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ለሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነሮች ያለኝን ታላቅ ምስጋና አቀርባለሁ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን በማሳተፍ ከሥር ወደ ላይ በዘለቀው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ላይ የተመሰረተው ይህ ጉባኤ፣ በቀላሉ የማይደገም እና በኢትዮጵያ ዘመናዊ ታሪክ ውስጥ ግዙፍና ታላቅ ዓላማ ያለው ነው:: በዚህም ፈተናዎቻችንን ወደ መልካም አጋጣሚዎች በመቀየር ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ባህልን እናጸናለን:: በዛሬው ዕለት ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ መልካም ዘሮችን እንዘራለን፤ ከሚያፈራውም ፍሬ ልጆቻችን እንዲጠቀሙ እናደርጋለን:: በዚህ ምክክር ላይ ስንሳተፍ ከየሰፈራችን ወጥተን ለኢትዮጵያ ስንመክር፣ ለልጆቻችን ስንልና እነርሱን እያሰብን ስንወያይ ውጤቱ እጅግ ፍሬያማ ይሆናል። አብረን ተስፋን፣ ይቅርታን እና በጋራ መኖርን እንትከል፤ በሀገር ውስጥ በሚደረግ ውይይትና ይቅርታ ችግሮቻችንን በመፍታት ሀገራችንን ከውጭ ጣልቃ ገብነት እንጠብቅ። ተሳታፊዎች በሙሉ ለኢትዮጵያ መልካም፣ ለአፍሪካ አስተማሪ፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን ደግሞ እውነተኛ እረፍትን የሚያመጣ ታሪካዊ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ጥሪዬን አቀርባለሁ:: ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!