Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-07-14 06:16

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

At this critical historical moment when Ethiopia is preparing for the historic and great national consultation. I have a great and noble call to convey to all the children of my country. The discussion that will start tomorrow is not only a perfect political platform, but also a new chapter in history that will completely determine our fate and future prospects. All those who are committed to the lasting peace, stability and universal prosperity of our country, who care about the greatness of Ethiopia; Here is the horse and the field! Just as our fathers and mothers fell in Adwa yesterday with their blood and bones for the country's freedom, sovereignty and glory, today Ethiopia is looking for its dedicated children who will carry the legacy of history. However, what our country needs today is not those who carry guns, but peace fighters who are armed with maturity, truth, knowledge and perseverance. We are on the eve of a great victory today as yesterday. Because Ethiopia and its people are bound to win! Through civilized speech, peaceful dialogue and national understanding, we will overcome all the challenges we face and move towards prosperity together!

Notes

ኢትዮጵያ ለታሪካዊውና ታላቁ የሀገራዊ ምክክር በምትሰናዳበት በዚህ ወሳኝ ታሪካዊ ወቅት፤ ለመላው የሀገሬ ልጆች የማስተላልፈው ታላቅና የከበረ ጥሪ አለኝ። ነገ የሚጀመረው ውይይት ፍቱን የፖለቲካ መድረክ ብቻ ሳይሆን፣ የእኛን እና የመጪውን ትውልድ እጣ ፈንታና የወደፊት ተስፋ ሙሉ በሙሉ የሚወስን አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ጭምር ነው። ‎ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም፣ መረጋጋትና ሁለንተናዊ ብልጽግና የምትተጉ፣ የኢትዮጵያ ታላቅነት ግድ የሚላችሁ ሁሉ፤ ፈረሱም ሜዳውም ይኸው! ‎ትናንት አባቶቻችንና እናቶቻችን በዓድዋ ለሀገር ነጻነት፣ ለሉዓላዊነትና ለክብር ሲሉ በደማቸውና በአጥንታቸው እንደተዋደቁላት ሁሉ፣ ዛሬም ኢትዮጵያ የታሪክ አደራ የሚሸከሙ የቁርጥ ቀን ልጆቿን ትፈልጋለች። ሆኖም ዛሬ ሀገራችን የምትሻው ጠመንጃ ያነገቡ ሳይሆን በሀሳብ ብስለት፣ በእውነት፣ በዕውቀትና በጽናት ታጥቀው የተሰናዱ የሰላም ታጋዮችን ነው። እኛ ዛሬም እንደ ትናንቱ በታላቅ የድል ዋዜማ ላይ እንገኛለን፤ ምክንያቱም የኢትዮጵያና የሕዝቦቿ ማሸነፍ አይቀሬ ነው! ‎በሰለጠነ ንግግር፣ በሰላማዊ ውይይትና ሀገራዊ መግባባት የገጠሙንን ፈተናዎች በሙሉ አልፈን ወደ ብልጽግና በጋራ እንሻገራለን!