Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-07-12 09:19

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

The King Tekle Religion Airport, which has been eagerly awaited by the people of Debre Markos for years and has been suspended for 30 years; It has been modernized and built to a higher standard and we officially inaugurated it today. Built on a length of 2,400 meters and a width of 30 meters, it has created a large capacity to land large passenger and cargo planes such as the Q400 and B737. The opening of this airport will greatly stimulate the business, investment and tourism activities of the area and will open a new chapter for the economic development of the area and the entire country. By turning challenges into opportunities; We will continue to demonstrate our determination to answer the development questions of our people step by step and to complete the mega projects we have started with quality and speed.

Notes

የደብረ ማርቆስና የአካባቢው ሕዝብ ለዓመታት በጉጉት ሲጠብቀው የነበረውና ለ30 ዓመታት ያህል ተቋርጦ የነበረው ንጉሥ ተክለ ሃይማኖት የአውሮፕላን ማረፊያ፤ በዘመናዊ መልክ ተሻሽሎና ደረጃው ከፍ ብሎ ተገንብቶ ዛሬ በይፋ አስመርቀናል። በ2,400 ሜትር ርዝመትና 30 ሜትር ስፋት ላይ የተገነባው እንደ Q400 እና B737 ያሉ ግዙፍ የሕዝብና የጭነት አውሮፕላኖችን ማሳረፍ የሚያስችል ከፍተኛ ዐቅምም ፈጥሯል። ይህ አውሮፕላን ማረፊያ ሥራ መጀመሩ የአካባቢውን የንግድ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም እንቅስቃሴ በከፍተኛ ሁኔታ በማነቃቃት ለአካባቢው እና ለመላው ሀገራችን የኢኮኖሚ ዕድገት አዲስ ምዕራፍ ይከፍታል። ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር፤ የሕዝባችንን የልማት ጥያቄዎች ደረጃ በደረጃ ለመመለስና የጀመርናቸውን ሜጋ ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት አጠናቆ ለምርቃት ለማብቃት ያለንን ቁርጠኝነት በተግባር እያሳየን እንቀጥላለን።