Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Ethiopia continues to perform! The Arbamanq Conference Resort, which we inaugurated today, is another great achievement of our 'Map for Generation' programme. This state-of-the-art resort includes a meeting hall that can accommodate over 1,300 people and a unique floating restaurant built on the lake. It will strengthen our goal of making Ethiopia the center of international forums by expanding conference tourism beyond our capital. It has also created a wide range of employment opportunities for the local community. I call on the entire people of our country, the diaspora and the international community to visit and use this new gem of our country, and to jointly support Ethiopia's new tourism and conference phase!
Notes
ኢትዮጵያ ማከናወኗን ቀጥላለች! ዛሬ ያስመረቅነው የአርባምንጭ ኮንፈረንስ ሪዞርት የ‘ገበታ ለትውልድ’ መርሃ-ግብራችን ያፈራው ሌላኛው ታላቅ ስኬት ነው። ይህ ዘመናዊ ሪዞርት ከ1,300 በላይ ሰዎችን የሚያስተናግድ የስብሰባ አዳራሽና በሐይቅ ላይ የተገነባ ልዩ ተንሳፋፊ ሬስቶራንትን ያካተተ ሲሆን፤ ከመዲናችን ባሻገር የኮንፈረንስ ቱሪዝምን በማስፋፋት ኢትዮጵያን የዓለም አቀፍ መድረኮች ማዕከል የማድረግ ርዕያችንን ያጠናክራል፤ ለአካባቢው ማኅበረሰብም ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጥሯል። መላው የሀገራችን ሕዝብ፣ ዳያስፖራውና የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ይህንን አዲስ የሀገራችንን ዕንቁ ስፍራ በመጎብኘትና በመጠቀም፣ የኢትዮጵያን አዲስ የቱሪዝምና የኮንፈረንስ ምዕራፍ በጋራ እንድንቋደስ ጥሪዬን አቀርባለሁ!