Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-07-03 11:19

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Today we have seen the rapid construction progress of the prestressed road project. The 29 km project comprising 22 km Kano-Jancha road and 7 km Ezo-Gircha branch road is progressing well, 13.3 km work has been completed. When the road is fully completed, it will further strengthen community ties, streamline trade and travel, and accelerate local economic development. ‎ During this visit, we visited the restored Dorze Lodge tourism destination, which has been under strong leadership of the community since 1997. On an area of ​​40,000 square meters, this wonderful place, resting on a cold and chained mountain range, offers a beautiful view that clearly shows the Abaya and Chamo lakes as well as the natural wonder known as the "Egzer Bridge". ‎ The development of road infrastructure alongside tourist destinations such as Dorze Lodge will help the area to fully utilize its enormous economic and cultural potential. Therefore, I call on Ethiopians living in the country and abroad, members of the diaspora, as well as visitors from all over the world to visit this amazing natural beauty and rich cultural heritage and become a sharer of the story.

Notes

የጫኖ-ጨንቻ መንገድ ፕሮጀክት የደረሰበትን ፈጣን የግንባታ ሂደት ዛሬ ተመልክተናል። የ22 ኪሎ ሜትር የጫኖ-ጨንቻ መንገድ እና የ7 ኪሎ ሜትር የኤዞ-ጊርጫ ቅርንጫፍ መንገድን የያዘው የ29 ኪሎ ሜትር ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ሲሆን፣ 13.3 ኪሎ ሜትር ስራው ተጠናቋል። የመንገዱ ስራ ‎ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የማኅበረሰቡን ትስስር ይበልጥ ያጠናክራል፣ ንግድ እና ጉዞን ያቀላጥፋል፣ እንዲሁም የአካባቢውን የኢኮኖሚ ልማት ያፋጥናል። ‎ ‎በዚሁ ጉብኝታችን፣ ከ1997 ዓ.ም ጀምሮ በማህበረሰቡ ጠንካራ መሪነት የያዘውና የታደሰውን የዶርዜ ሎጅ የቱሪዝም መዳረሻ ጎብኝተናል። በ40 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ ላይ፣ በቀዝቃዛውና ሰንሰለታማ የተራራ ጋራ ላይ ያረፈው ይህ አስደናቂ ሥፍራ፣ የአባያና ጫሞ ሐይቆችን እንዲሁም “የእግዜር ድልድይ” ተብሎ የሚጠራውን የተፈጥሮ ድንቅ ዕይታ በአንድ ላይ በግልጽ የሚያሳይ ውብ ገጽታን ይሰጣል። ‎ ‎እንደ ዶርዜ ሎጅ ያሉ መሰል የቱሪስት መዳረሻዎች ጎን ለጎን የሚከናወነው የመንገድ መሠረተ-ልማት መስፋፋት፣ ስፍራው ያለውን እጅግ ከፍተኛ የኢኮኖሚና የባህል አቅም ሙሉ በሙሉ አውጥቶ ለመጠቀም በእጅጉ ያግዛል። በመሆኑም፣ በሃገር ውስጥ እና በውጭ ሃገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና የዲያስፖራ አባላት፣ እንዲሁም ከመላው ዓለም የሚመጡ ጎብኚዎች ይህንን አስደናቂ የተፈጥሮ ውበትና የበለጸገ የባህል ሐብት እንዲጎበኙና የታሪኩ ተጋሪ እንዲሆኑ ጥሪዬን አቀርባለሁ።