Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-07-03 14:01

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Arbaminch; Its development resources continue to grow! ‎ Today we visited the Kuriftu Resort and Spa, which is located on an area of 52,000 square meters in the city of Arba Mojang. ‎ This grand project includes 53 luxury villas and will create permanent employment opportunities for more than 300 citizens. Such investments are a clear indication of the great contribution that the private sector can make following the infrastructure built by the government. ‎ I am calling on local and foreign investors to expand and invest in Ethiopia in such great projects that will take our country's tourism potential to the next level!

Notes

አርባ ምንጭ፤ የልማት ምንጭነቷ እየጎመራ ቀጥሏል! ‎ ‎በአርባ ምንጭ ከተማ በ52,000 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈውን የኩሪፍቱ ሪዞርት እና ስፓ ዛሬ ጎብኝተናል። ‎ ‎ይህ ታላቅ ፕሮጀክት 53 ቅንጡ ቪላዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከ300 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች ቋሚ የሥራ ዕድል ይፈጥራል። መሰል ኢንቨስትመንቶች የመደመር መንግሥት የገነባቸውን መሠረተ-ልማቶች ተከትሎ የግሉ ዘርፍ ማበርከት የሚችለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በግልጽ የሚያሳይ ነው። ‎ ‎የሀገራችንን የቱሪዝም አቅም ወደ ላቀ ምዕራፍ የሚያሸጋግሩ መሰል ታላላቅ ፕሮጀክቶች ላይ፣ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በስፋት እንዲሰማሩና መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪዬን አቀርባለሁ!