Announcement
Abiy Ahmed  ·  2026-06-28 15:53

Telegram @AbiyAhmedAliOfficial

Today, we officially inaugurated the 87.6-hectare, 10.5-kilometer-long Enteto-Kepena river and riverbank development project. This extensive infrastructure includes river defense walls, modern bridges and extensive green spaces. The project is not only a construction success, but it is also a great opportunity to accelerate our strategic transition to make our capital a climate-resilient and convenient for its residents, an international tourism and economic center. ‎ We will continue the journey we started to improve the quality of life of our citizens and bring fundamental change by fulfilling the public trust given to us with honesty, hard work and sincerity!

Notes

87.6 ሄክታር መሬት የሚሸፍነውን እና 10.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውን የእንጦጦ-ቀበና የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ፕሮጀክትን ዛሬ በይፋ መርቀናል። ይህ ሰፊ መሰረተ ልማት የወንዝ መከላከያ ግንቦችን፣ ዘመናዊ ድልድዮችን እና ሰፊ አረንጓዴ ስፍራዎችን በጋራ የያዘ ነው። ፕሮጀክቱ የግንባታ ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ መዲናችንን የአየር ንብረት ለውጥን የምትቋቋምና ለነዋሪዎቿ ምቹ የሆነች፣ ዓለም አቀፍ የቱሪዝም እና የኢኮኖሚ ማዕከል ለማድረግ የጀመርነውን ስልታዊ ሽግግር የሚያፋጥን ታላቅ አጋጣሚ ነው። ‎ ‎የተሰጠንን ሕዝባዊ አደራ በታማኝነት፣ በጽኑ ትጋት እና በቅንነት በመፈጸም የዜጎቻችንን የኑሮ ጥራት ለማሻሻልና መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት የጀመርነውን ጉዞ አበክረን እንቀጥላለን!