Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Today, we officially launched Africa's first integrated digital service application, which combines services provided by various institutions in one platform, at a conference called 'Digital for Excellence'. This great achievement is a source of great pride for our country and proof of what technology-driven and purpose-driven investment can achieve. Mesob, which is an important infrastructure of the economy, is a one-center service. It saves citizens' time, closes the loopholes of corruption, and strengthens the integrity and strength of institutions on the part of the government. Above all, it is a clear testimony that Ethiopia's dreams are not mere wishes, but realities that we can build with our own hands and capabilities. I call upon us to strengthen this success, to share our experience with our African brothers and sisters, and to be determined to achieve more results!
Notes
'‘ዲጂታል ለልህቀት'’ በሚል ስያሜ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ፣ በተለያዩ ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በአንድ መድረክ የሚያጣምረውን፣ በአፍሪካ ቀዳሚ የተቀናጀ የዲጂታል አገልግሎት መተግበሪያ ዛሬ በይፋ መርቀናል። ይህ ታላቅ ስኬት ለሀገራችን ከፍተኛ ኩራት ከመሆኑም በላይ በቴክኖሎጂ የሚመራ እና ዓላማ ተኮር ኢንቨስትመንት ምን ሊያስገኝ እንደሚችል ማረጋገጫ ነው። የኢኮኖሚ ወሳኝ መሠረተ ልማት የሆነው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፤ የዜጎችን ጊዜ ይቆጥባል፣ የሙስና ቀዳዳዎችን ይደፍናል፣ እንዲሁም በመንግሥት በኩል የተቋማትን ታማኝነትና ጥንካሬ ያጎለብታል። ከሁሉም በላይ የኢትዮጵያ ትልሞች ተራ ምኞት ሳይሆኑ፣ በራሳችን እጆችና አቅም የምንገነባቸው እውነታዎች መሆናቸውን በግልጽ የሚያሳይ ምስክር ነው። ይህን ስኬት እንድናጠናክር፣ ተሞክሯችንን ለአፍሪካውያን ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንድናካፍል፣ እንዲሁም ከዚህ የበለጠ ውጤት ለማስመዝገብ በቁርጠኝነት እንድንጓዝ ጥሪዬን አቀርባለሁ!