Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Following our Council of Ministers meeting, we visited a construction site that showcased houses built using the latest and fastest technological resources. Three advanced construction methods were used in combination on this site; 3D printing, prefabricated lightweight steel construction and container housing. Each of these builds has proven that speed and quality are not mutually exclusive when using the right technology; They are living proof that quality homes can be completed in days and weeks instead of months and years. This type of advanced innovation can be easily implemented, replicated and expanded in any part of the country, so it has the power to significantly change the direction of our country's housing development program. We have combined technology with our national theme. Our works that have been demonstrated in practice have shown that we are moving in the right direction with determination to realize the rapid development that the country deserves!
Notes
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባችንን ተከትሎ፣ እጅግ ዘመናዊና ፈጣን የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን በመጠቀም የተገነቡ ቤቶችን የሚያሳይ የግንባታ ሳይት ጎብኝተናል። በዚህ ሳይት ሦስት የላቁ የግንባታ ዘዴዎች በጥምረት ጥቅም ላይ ውለዋል፤ የ3ዲ ህትመት(3D printing)፣ የቅድመ-ዝግጅት ቀላል የአረብ ብረት ግንባታ እና የኮንቴይነር መኖሪያ ቤቶች ናቸው። እያንዳንዳቸው ግንባታዎች ትክክለኛውን ቴክኖሎጂ ስንጠቀም ፍጥነት እና ጥራት እርስ በእርስ የማይጋጩ መሆናቸውን ያረጋገጡ ሲሆን፤ ጥራታቸውን የጠበቁ መኖሪያ ቤቶችን ከወራትና ከዓመታት ይልቅ በጥቂት ቀናት እና ሳምንታት ውስጥ ሰርቶ ማጠናቀቅ እንደሚቻል የታየበት ህያው ምስክር ናቸው። ይህ አይነቱ የላቀ ፈጠራ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል በቀላሉ ሊተገበር፣ ሊደገም እና ሊስፋፋ የሚችል በመሆኑ የሀገራችንን የቤት ልማት ፕሮግራም አቅጣጫ በከፍተኛ ደረጃ የመቀየር ኃይል አለው። ቴክኖሎጂን ከሀገራዊ ርዕያችን ጋር አጣምረናል፤ መሰል በተግባር የተገለጡ ስራዎቻችን ደግሞ ለሀገር የሚገባውን ፈጣን እድገት እውን ለማድረግ በትክክለኛው አቅጣጫ ላይ በቁርጠኝነት እየተጓዝን መሆናችንን በተግባር አሳይቷል!