Telegram @AbiyAhmedAliOfficial
Dear Ethiopians, congratulations on the milestone of 5 million coders! The goal that was planned to be achieved in three years was achieved in less than two years. "5 million Ethiopian coders" on July 16, 2016. Since its inception, 5,005,146 trainees have registered and more than 3 million have completed the training in computer programming, data analysis, Android software development and artificial intelligence fundamentals. This achievement is a testament to the determination and boundless potential of our people. The historical phase that we started to prepare for the digital world. It is not the end of our journey, but it is the starting point to further accelerate our national goal. Until August 2018 I call on every Ethiopian to be a part of this national mission in order to reach the goal of reaching 7 million trainees. For our young students. The coming winter season is your big chance. Avoid wasting your time. When you return to school by enrolling and learning, I urge you to become not just students, but globally recognized digital leaders. The trainings are completely free and the certification is internationally recognized. The tomorrow you build starts today! Click here to register. ethiocoders.et/
Notes
ውድ ኢትዮጵያውያን ለ5 ሚሊዮን ኮደሮች ምዕራፍ ስኬት እንኳን ደስ አላችሁ! በሦስት ዓመታት ውስጥ ለማሳካት የታቀደውን ግብ ከሁለት ዓመት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ማሳካት ተችሏል። የ«5 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች» ሐምሌ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በኮምፒውተር ፕሮግራሚንግ፣ በመረጃ ትንተና፣ በአንድሮይድ ሶፍትዌር ልማት እና በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ ትምህርቶች 5,005,146 ሰልጣኞች ተመዝግበው ከ3 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀዋል። ይህ ስኬት የሕዝባችንን ቁርጠኝነት እና ወሰን የሌለው አቅም ማረጋገጫ ነው። በዲጂታሉ ዓለም በልኩ ለመዘጋጀት የጀመርነው ታሪካዊ ምዕራፍ፤ የጉዟችን ማብቂያ ሳይሆን፥ ብሔራዊ ርዕያችንን ይበልጥ የምናፋጥንበት መነሻ ነው። እስከ ነሐሴ 2018 ዓ.ም. ድረስ የሰልጣኞችን ቁጥር 7 ሚሊዮን ለማድረስ የተሰነቀውን ግብ ለማሳካት፥ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የዚህ ብሔራዊ ተልዕኮ አካል እንዲሆን ጥሪዬን አቀርባለሁ። ለወጣት ተማሪዎቻችን፤ መጭው የክረምት ወቅት ትልቅ ዕድላችሁ ነው። ጊዜያችሁን በዋዛ ከማሳለፍ ተቆጥባችሁ፤ በመመዝገብና በመማር ወደ ትምህርት ገበታችሁ ስትመለሱ ተማሪዎች ብቻ ሳትሆኑ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላችሁ የዲጂታል መሪዎች እንድትሆኑ አሳስባለሁ። ሥልጠናዎቹ ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጡ ሲሆን፥ የምስክር ወረቀቱም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ነው። የምትገነቡት ነገ የሚጀምረው ዛሬ ነው! ለመመዝገብ እዚህ ይጫኑ: ethiocoders.et/